ጭነትዎን ቀልጣፋ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ያጓጉዙ!

መተግበሪያችንን አሁኑኑ አውርደው ከጭነት እስከ ርክክብ ያለውን የጭነትዎን ሂደት ያቀላጥፉ።

ለአስጫኞች የሚሰጠው ጥቅም ለአጓጓዦች የሚሰጠው ጥቅም

ስለ ፎርዋርድ ሎጅስቲክስ

ፎርዋርድ ሎጅስቲክስ ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት መሰረት የሆነውን የትራንስፖርት ዘርፍ በማዘመን በዘርፉ በዋናነት የሚጠቀሱት የእቃ አስጫኞችን ፣ ሹፌሮችን እና አጓጓዦችን ትርፋማነት እና ውጤታማነት ለማሳደግ የተቋቋመ የቴክኖሎጂ ተቋም ነው።

የምንሰጠው አገልግሎት

ፎርዋርድ ሎጅስቲክስ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ፣ ቀልጣፋ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ግልጽ የሆነ የሎጅስቲክስ አገልግሎት በሀገር ደረጃ ይዞ ቀርቧል።


አገልግሎቱ ለአሰራር ውስብስብ እና አስቸጋሪ የሆነውን የሎጅስቲክስ ችግር ለመፍታት እንዲሁም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ህልም እውን ለማድረግ ያስችላል።

የምንሰጠው አገልግሎት ለአስጫኞች የሚሰጠው ጥቅም

  • አስጫኞች የፈለጉትን አጓጓዥ በዋጋ ፣ በመኪና አይነት ፣ ልምድ እና በመሳሰሉት መስፈርት አወዳድረው ማስጫን የሚችሉበት መንገድ መኖሩ።
  • ግልጽ በሆነ አሰራር ጭነትዎ ሲጫን ፣ ሲጓጓዝ እና ሲራገፍ መከታተል እንዲችሉ በማድረግ ጭነትዎ እንዳይሰረቅ (እንዳይቀሸብ) ለመቆጣጠር ያስችላል።
  • ጭነቶችን ከፈለጉ አሁን አልያም ወደፊት አቅደው ማስጫን የሚችሉበት አማራጭ መኖሩ።
  • ህጋዊነታቸው የተረጋገጡ አጓጓዥ እና ሹፌሮችን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል።
  • ለጭነትዎ ኢንሹራንስ ያለው አጓጓዥ እንዲያገኙ ያስችላል።
  • ስለሚያገኙት አገልግሎት በቴክኖሎጂ (እጅዎት ላይ ባለ ስልክ ወይንም ጥሪ ማዕከል) የታገዘ መረጃን ማግኘት የሚችሉበት።
  • እቃዎች ሲጫኑ እና ሲራገፉ ያሉበት ሁኔታን በመመዝገብ በኋላ ከሚፈጠር ጭቅጭቅ ይታደጋል።
  • አገልግሎት ስለሚሰጥዎት አሽከርካሪ እና አጓጓዥ የስራ አፈጻጸም ሪከርድ የሚያገኙበት።
  • አስጫኝ አገልግሎቱን ካገኘ በኃላ ስለ አጓጓዥ እና ሹፌሩ የስራ አፈጻጸው አስተያየት መስጠት የሚችሉበት።
  • አንድ ላይ መጫን የማይችሉ ጭነቶች አብረው እንዳይጫኑ መቆጣጠሪያ ዘዴ ይዞ የመጣ።

የምንሰጠው አገልግሎት ለሹፌሮች የሚሰጠው ጥቅም

  • አሽከርካሪዎች የጭነት እቅዶቻቸውን እንዲቆጣጠሩ በማገዝ በባዶ የመመለስ አጋጣሚዎችን ይቀንሳል።
  • አሽከርካሪዎች ጭነት እንዲያገኙ በማድረግ ስራ በማጣት ከሚመጣ ኪሳራ ይታደጋል።
  • አሽከርካሪዎች የሚጭኑትን እቃ ዝርዝር መረጃ ማለትም የሚጫነውን እቃ ምስል፣ ብዛት፣ አይነት እና የመሳሰሉትን መረጃዎች እንዲያገኙ ያስችላል።
  • የጭነት መልቀቂያ እና መረከቢያ ቅጾችን ለህግ አግባብ ምቹ በሆነ ሁኔታ ያዘጋጃል።
  • ተሽከርካሪው የሚያስገባውን ገቢ ለመከታተል ያስችላል።
  • አሸከርካሪዎች የሚጭኑትን እቃ ምንንነት አስቀድመው እንዲያውቁ በማድረግ ጭነቶችን መርጠው እንዲቀበሉ ያግዛል።
  • እቃዎች ሲጫኑ እና ሲራገፉ ያሉበት ሁኔታ በመመዝገብ በርክክብ ጊዜ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ያስወግዳል።
  • አሽከርካሪዎች ለጠፍ የጭነት ሂደቶችን በተገባ ሁኔታ እንዲያሳልጡ ያግዛል።

መተግበሪያዎቻችን

ምን ይጠብቃሉ? አሁኑኑ መተግበሪያዎቻችንን አውርደው ጭነትዎን ያቀላጥፉ!

Forward Consignor
Forward Driver
Forward Transporter

ያግኙን

አድራሻ

ቦሌ ሩዋንዳ ከቲዜድ ሆቴል አጠገብ፣ 3ኛ ፎቅ
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

ስልክ.ቁ

+251116663766

ኢሜይል

info@matrixet.com

የስራ ሰዓት

ከሰኞ እስከ አርብ
2:30 - 11:00